በማንም ተጽእኖ የለለበት ነጻ የአእምሮ ጤና ውክልና/ Independent Mental Health Advocacy (IMHA) መብትዎን እንዲያውቁ እና ሀሳብዎን እንዲገልጹ ሊረዳዎት ይችላል።
IMHA ነጻ እናምስጢራዊ የጥብቅና አገልግሎት ሲህን፣ አገልግቱን የሚያገኙት፡
- የግዴታ ህክምና እየተደረገላቸው ላሉት
- ወይም የግዴታ ህክምና ማግኘት ለሚያስጨንቃቸው ይሆናል።
IMHA በቪክቶሪያ ሊጋል ኤይድ የሚሰጥ አገልግሎት ቢሆንም የህግ አገልግሎት አይደለም። IMHA ነፃ የሆነ እና ከአእምሮ ጤና የተለየ አገልግሎት ነው።
እናነጋግርዎታለን
ከመስከረም 1 ቀን 2023 ዓ.ም ጀምሮ የአእምሮ ጤናና ደህንነት ደንብ 2022 (ቪክ)/Mental Health and Wellbeing Act 2022 (Vic) እንደሚለው የግዴታ ህክምና በምታደርጉበት ጊዜ ቁልፍ ነጥቦችን ለእኛ እንደሚገልጹልን በግልጽ ተቀምጧል። ስለ 'IMHA መቼ እንደሚገለጽለት/‘when will IMHA be notified?’ በበለጠ ይወቁ።
እንዳናናግርዎ ካልነገሩን በስተቀር እናነጋግርዎትአለን። ከእርስዎ ጋር ስንገናኝ ምን እንደምናደርግ እናስረዳዎትአለን፤ እንዲሁም የእኛን አገልግሎቶች ማግኘት የሚፈልጉ ከሆነ መወሰን ይችላሉ። እንዳንገናኝዎት ከፈለጉ እንዴት ማነጋገር እንዳለብዎ ይወቁ።
እርስዎ እኛን ማነጋገር ይችላሉ
በአሁኑ ጊዜ የግዴታ ህክምና የማያካሂዱ ከሆነ፣ ነገር ግን የግዴታ ህክምናውን ለማግኘት የሚጨነቁ ከሆነ፣ አሁንም የ IMHA አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ። ሰለጉዳዩ ስለማይነገረን እኛን በቀጥታ እንዲያነጋግሩን ይገባል። በስልክ 1300 947 820 መደወል ይችላሉ። ወይም ኢሜይል contact@imha.vic.gov.au ይላኩልን።እንዴት እኛን ማነጋገር እንደሚቻል በበለጠ ማወቅ። እንዲሁምበራስዎ ቋንቋ ከእኛ ጋር መነጋገር ይችላሉ።
ሰዎች የግዴታ ህክምና ስለመቀበል ሊጨነቁ የሚችሉባቸው የተለመዱ ምክንያቶች፣ ከህክምና አድራጊ ቡድን ጋር መቃረን እንደማይችሉ፣ ወይም የህክምና ቡድንዎ አንድ ነገር የማያደርጉ ከሆነ የበግዴታ ህክምና እንዲያደርጉ እንደሚያስገድዱዎ መጥቀሳቸውን ያካትታል።
IMHA እንዴት ሊረዳዎ እንደሚችል
በሚከተሉት መንገዶች እንረዳዎትአለን፡
- የግምገማዎን፣ የህክምናዎን፤ የእንክብካቤዎ እና የማገገም መረጃዎችን እንዲረዱ መርዳት
- የግምገማዎን፤ ህክምናዎን እና እንክብካቤ በተመለከተ ውሳኔዎች ስለማድረግ
- መብትዎን መረዳትና መጠቀም
- ምርጫዎችን አስቀድመው በጽሁፍ አድርጎ ማቅረብ/መግለጥ
- የመረጡትን የድጋፍ ሰጪ ሰው መሾም
- ሁለተኛ የስነ-አእምሮ ሙያተኛ ምርጫ ማማከር
- የህግ ምክር መጠየቅ
- ለአዕምሮ ጤና ልዩ ፍርድ ቤት (Mental Health Tribunal) ማመልከት
- የአዕምሮ ጤናን እና የደህንነት አገልግሎት ስርአትን መረዳትና ማግኘት
- ውሳኔዎን፤ አመለካከትዎን እና ምርጫዎን ለአዕምሮ ጤና እና ደህንነት አገልግሎት እና ለሌሎችም መግለጽ
- ቅሬታ ማቅረብ ናቸው።
አስተርጓሚ ማዘጋጀት እንችላለን፤ ስለዚህ በራስዎ ቋንቋ ያነጋግሩናል። በተጨማሪም በ 131 450 የትርጉምና የትርጁማን አገልግሎት ስልክ ደውለው ከእኛ ጋር እንዲያገናኙዎት መጠየቅ ይችላሉ።
IMHA በእርስዎ ፈቃድ ስለ አዕምሮ ጤና እና ደህንነት አገልግሎት ያለዎትን አመለካከት ወክሎ መናገር ይችላል።
የእርስዎ IMHA አቡካቶ፡
- በእርስዎ መመሪያ መሰረት እርምጃ መውሰድ
- ያለ ፈቃድዎ እርምጃ አንወስድም
- ቢያንስ እድሜዎ 16 ዓመት ከሆነ፣ ሌሎች እርስዎን በጣም ይጠጥቅማል ብለው በሚያስቡት ነገር አይመራም። ድሜዎ 15 ዓመት ወይም ከዚያ በታች ከሆነ IMHA የእርስዎን አመለካከት እንደሚያበረታታ እና የእርስዎን ጥቅም ለመጠበቅ ከእርስዎ፤ ቤተሰቦችዎ፤ ተንከባካቢዎችዎ እና ደጋፊዎችዎ ጋር አብሮ ይሰራል።
እንዳንገናኝዎት ከፈለጉ ይንገሩን
በሚከተሉት ጉዳዮች ላይ እርግጠኛ እንድንሆን፣ ስለ እርስዎየመለያ መረጃ ማቅረብ ይኖርብዎታል፡
- ከእርስዎ ጋር መገናኘት እንዳንሞክር፣ እና
- ስለ አስገዳጅ ህክምናዎ ያገኘነውን መረጃ እንድሰርዝ።
የሚሰጡን መረጃ በአስተዳደር ሰራተኞቻችን በኩል ይያዛል። የግል መረጃዎችን እንዴት እንደምንይዝ እና የግል ሚስጥርዎን እንደምንጠብቅ በበለጠ ማወቅ።
እንዳንገናኝዎት ለመናገር፡
- በስልክ ጥሪ (03) 9093 3701
- the በኦፕት-አውት/opt-out ቅጽ ላይ መሙላት
- ቅጹ አጠናቅቀው በኢሜል admin@imha.vic.gov.au ወይም በፖስታ አማካኝነት ይላኩ።
- Independent Mental Health Advocacy
ፖ.ሳ.ቁጥር/GPO Box 4380
Melbourne VIC 3001
- Independent Mental Health Advocacy
ቅጹን ሞልተው ለማቅረብ የሚረዳዎ ሠራተኛ ወይም ደጋፊ ሰጪ መጠየቅ ይችላሉ።
ሀሳብዎን ቆይተው ከቀየሩ የግዴታ ህክምና ሲደረግልዎ እና IMHA እንዲያነጋግርዎ የሚፈልጉ ከሆነ እንዲህ ማድረግ ይችላሉ፡
- በስልክ 1300 947 820 ይደውሉ
- በ contact@imha.vic.gov.au ኢሜል ያድርጉ
- እንዴት እኛን እንደሚያነጋግሩ በበለጥ ማወቅ።
ለIMHA መቼ ነው የሚነገር?
IMHA እንዲህ ከሆነ ይነገራል፡
- በጊዜያዊ የህክምና ትእዛዝ ወይም በህክምና ትእዛዝ ላይ ተቀምጠው ከሆነ፣ ይህም በህክምና ማጣሪያ ወይም የደህንነት ታማሚ መሆንን ጨምሮ
- በንግግር የመግባባት መብትዎ ከተገደበ
- ጊዜያዊ የህክምና ትእዛዝዎ ወይም የህክምና ትእዛዝዎ ከህብረተሰቡ ወደ የሆስፒታል ታካሚነት ወይም ከሆስፒታል ታካሚነት ወደ ማህበረሰብ ተቀይሮ ከሆነ
- ጊዜያዊ የህክምና ትእዛዝዎ ወይም የህክምና ስርዓትዎ ከተከለከለ ወይም ከተሰረዘ
- የአዕምሮ ጤና ልዩ ፍርድ ቤት የክርክር ቀጠሮ ካለዎት
- የገደብ ጣልቃ ገብነት ጥቅም ላይ ይውላል፣ ለምሳሌ፡ እንዲገለሉ ከተደረገ ወይም በአካል ወይም በኬሚካል ታግተው ከሆነ
- የዝውውር ተእዛዝዎ ለህክምና ወደ ሌላ የአእምሮ ጤና አገልግሎት ሄደው እንዲታከሙ ተቀይሮ ከሆነ ነው።
የደህንነት ታማሚ ከሆኑ IMHA ሊነግርዎት የሚችለው፡
- የተመደበ የአእምሮ ጤና አገልግሎት ለህክምና ከተቀበለዎት ወይም ወደዚያ ክተጓጓዙ
- ወደ እስር ቤት እንዲመለሱ ከሆስፒታል ከወጡ።
የህክምና ምርመራ ታካሚ ከሆኑ IMHA ሊነረው የሚችለው፡
- ወደ ተወሰነ የአዕምሮ ጤና አገልግሎት ክተጓጓዙ፣ የምርመራ ፎረንሲክ ፈቃድ ፓነል/ቡድን (Forensic Leave Panel) መጓጓዝዎን ካጸደቀ ወይም በሌላ መንገድ በተፈቀደለት አካል መመሪያ ከተሰጠ ይሆናል
- የስነ አእምሮ ሀኪምዎ ወይም ዋናው የስነ አእምሮ ሀኪም ወደ ሌላ የተመደበ የአእምሮ ጤና አገልግሎት እንዲጓጓዙ መመሪያ ከሰጠ
- ፎረንሲካሬ (Forensicare) ለአእምሮ ልዩ ጤና ፍርድ ቤት (Mental Health Tribunal) ከፍተኛ ክትትል የሚደረግበት ትእዛዝ፣ ይህ ትእዛዝ ከተላለፈና መቼ እንደሆነ ሲመለከት ይሆናል።
ለ IMHA መረጃ ጽሁፋዊ ወረቀት የ(ኦፕት=አውት/opt-out ቅጽን) ተጭኖ ማውጣት
የ IMHA መረጃ ወረቀት (ኦፕት=አውት/opt-out ቅጽ)
ለ IMHA ፖስት ካርድ ተጭኖ ማውጣት
IMHAን እንዴት ማነጋገር እና ተጨማሪ መረጃ ማግኘት እንደሚቻል
- በኢሜል contact@imha.vic.gov.au ይላኩ።
- ለIMHA በስልክ ቁጥር 1300 947 820 ይደውሉ። ይህም IMHA ወኪል ሰራተኛ ከጥዋቱ 9.30 am እስከ ከሰዓት በኋላ 4.30 pm በሳምንት ሰባት ቀናት (ከህዝባዊ በዓላት በስተቀር) ይገኛሉ። በራስዎ ቋንቋ እኛን ማነጋገር ይችላሉ።
- ስለ መብትዎ የድምጽ ቅጂ ለመስማት በስልክ 1800 959 353 ላይ ለIMHA መብት መስመር ይደውሉ።
- እንዴት cእኛን ማነጋገር እንደሚችሉ በበለጠ ማወቅ።
- IMHAን ለማነጋገር እንዲረዳዎት የአእምሮ ጤና አገልግሎት ሰጪ፣ ተንከባካቢ ወይም ሌላ ድጋፍ ሰጪን ይጠይቁ።
- ስለ IMHA አስተያየት መስጠት ወይም ቅሬታ ማቅረብ የሚፈልጉ ከሆነ፣ እባክዎ እኛን ያነጋግሩ። ስለ ቅሬታ እና አስተያየት መስጠት በበለጠ ይወቁ።
More information
Updated